Fana: At a Speed of Life!

በሩሲያና እና ቤላሩስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በሩሲያና እና ቤላሩስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እና በዳያስፖራው ተሳትፎ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::

በውውይቱ  ወቅት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የመልሶ ግንባታ ጥረት እና ሰብአዊ እርዳታ፣ ከሱዳን ጋር ስላለው የድንበር ጉዳይና ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁኔታ ውይይት ተደርጓል።

ከዚህ ባለፈም ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነታዎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያም ገለፃ እና ውይይት መደረጉ ነው የተመላከተው።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ዳያስፖራዎችም ያሏቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች  አንስተዋል።

በዚህም የህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ እና የኢትዮጵያን  ወቅታዊ እውነተኛ ገፅታ በማህበራዊ መገናኛ መረቦች እና በሌሎች መንገዶች በማስተዋወቅ  እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ  በማድረግ እንደሚሳተፉ መግለጻቸውን በሞስኮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.