Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ማርቆስ ከተማ ተከስቶ ነበረው የእሳት አደጋ በህብረተሰቡ እና በወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ ተከስቶ ነበረው የእሳት አደጋ በህብረተሰቡ እና በወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡
አደጋው ዛሬ ከጠዋቱ 12:40 አካባቢ ቀበሌ ዐ1 ልዩ ቦታው ቄራ የደረሰ ሲሆን የንብረት ውድመት አድርሷል ።
የአደጋው መጠንና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅም ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
እሳቱን ለማጥፋት፣ወደ ሌላ ሱቆችና ወደ መናኸሪያ እንዳይዛመት እንዲሁም በቁጥጥር ስር ለማዋል የተለያዩ አካላት ፣የከተማው ማህበረሰብና ወጣቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡
በአሁኑ ሰአትም የእሳት አደጋውን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.