Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞንና በሚዛን አማን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞንና በሚዛን አማን ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

ከጉራጌ ዞን ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየሰጡት ያለውን የለውጥ አመራርና ስኬቱን በማድነቅ እንዲሁም ከጎናቸው መቆማቸውን በማረጋገጥ በቡታጅራ ከተማ የድጋፍ ሠልፍያካሄዱት፡፡

ሰልፈኞቹ  ‘ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት  ይጠናከራል፣  ከብልጽግና ጋር ስኬታማ እንሆናለን፤  በጁንታው መቃብር ላይ ብልጽግና ፣ ሠላምና የሕዝቦች አንድነት ይለመልማል’  የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች አስተላልፈዋል፡፡

በተመሳሳይ የቤንች ሸኮ ዞን ነዋሪዎች በሚዛን አማን ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን የሰልፉ አላማ ሀገሪቱ የያዘችውን የለውጥ ጉዞ ለመቀልበስ የውጭና የሀገር ውስጥ ውጥረት የሚፈጥሩ አካላት በተበራከቱበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና አመራራቸው ሀገሪቱን ከመበታተን ለማውጣት ላደረጉት የአመራር ቁርጠኝነት ለማድነቅና ከጎናቸው ለመቆም የታሰበ ነው ተብሏል።

በተስፋዬ አይጠገብ ተጨማሪ መረጃ ከደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.