Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የስድስት ወራት ዋና ዋና የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዋና ዋና የስራ ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

የሕግ የበላይነት እንዲከበር ሕገ መንግስታዊ ውሳኔዎችን ማሳለፍ መቻሉ፣ የ15ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል እኩልነትና ሕብረብሄራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በልዩ ሁኔታ መከበሩ፣ የወጣቶችእና ሴቶች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እና በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ላይ ምክር ቤቱ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱ ተነስቷል፡፡

በተያያዘም የመንግሥታት ግንኙነት ስርዓት አዋጅ እንዲወጣና መተግበር መጀመሩ በምክር ቤቱ አሰራር ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት መጀመሩ፣  የምክር ቤቱ ፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ ከማጠናከር አኳያ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች/ ከሩሲያ፣ ኳታር፤ ቻይና፤ ቱርክ እና ጀርመን/ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፣ ሕገ መንግስቱ ለሴቶች ያጎናፀፋቸው የእኩልነት መብት እንዲረጋገጥና ከፌደራል ስርዓቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሁሉም ከሚመለከታቸው አካላትጋር ምክር ቤቱ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለ22 ዓመታት ያህል ሳይሻሻል የቆየውና ግልጸኝነት የጎደለው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ተሻሽሎ በአዲሱ ግልጸኝነት ባለው መተካቱ የሃብት ክፍፍሉን ፍትሓዊነት እንዲረጋገጥ ጉልህ ሚና ከመጫወቱም በላይ የፌደራል ሥርዓቱ ጤናማነትና ቀጣይነት እንዲሁም በክልሎች መካከል ጤናማ ግንኙነት፣ ጠንካራ ሕብረብሔራዊ አንድነትና መተማመን እንዲጎለብት ድርሻው የጎላ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

አዲሱ የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቀመር የክልሎች የገቢ አሰባሰብ አቅም በብዙ እጥፍ እንዲጨምር ማድረጉም በጠንካራነቱ ተወስቷል።

በተጨማሪም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችም በሪፖርቱ የተቀመጡ ሲሆን ይህም የፌደራል የመሰረተ ልማት ፍትሃዊ ስርጭት ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀው የስርጭት መስፈርት ፍትሓዊነት ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ እንደሆነና ወደ ፊት በይበልጥ እንዲሻሻል፣ የለውጥ መሣሪያ ወይም የሪፎርም መሣሪያዎች ፣ መጠቀም ሁሉም ሰራተኞች በዕቅድ መሠረት መመዘንና መደገፍ እንደሚገባቸውም ተነስቷል ።

በተጨማሪም ሥራዎች በጥራት፣ በጊዜና በወጪ መሠረት መመዘን ላይ ጅምሮች ቢኖሩም ትኩረት የሚሹ መሆናቸውም በሪፖርቱ ተካቷል።

በተጨማሪም የምክር ቤቱንና ብሎም የሀገሪቱን መልካም ገጽታ መገንባት የሁሉም ዜጎች ተቀዳሚ ተግባር ቢሆንም በተለይም የመንግስት ሰራተኞች ግን ድርብ ሃላፊነት እንዳለባቸው መገለጹን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.