Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁሉም የቦርዱ አመራሮችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን በተገኙበት አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱን የተመለከተ ገለጻ ተደረገ።

መድረኩን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ራሔል ባፌ በንግግር የከፈቱት ሲሆን መጪውን ምርጫ አስመልክቶ የቦርዱን የሥራ ሂደትና ዝግጁነት በተመለከተ በተለያዩ የቦርዱ የሥራ ክፍሎች አማካኝነት ማብራሪያ እንደተሰጠበት ተገልጿል።

ይህውም ከቦርዱ የኦፕሬሽን ክፍል፣ ከቦርዱ የሲቪክና የመራጮች ትምህርት ክፍል፣ ከሥልጠና ክፍል፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍል እንዲሁም ከውጭ ግኑኝነትና ከሥርዓተ-ፆታ ክፍል ሲሆን የሥራ ክፍላቸውን ዝግጁነትና የሥራ ሂደቱን አሰመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ባለሞያዎች ናቸው ተብሏል።

ማብራሪያ ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል የዕጩዎች ምዝገባ ሂደትና መሥፈርቶች፣ የምርጫ ጉዳይ ዓለም ዓቀፍ ባለሞያ የዲጂታል የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ዋነኞቹ ናቸው፡፡

እንዲሁም የድምፅ መስጫ ወረቀት ዝግጁነትን አስመልክቶ በሌላ ዓለም ዓቀፍ የምርጫ ባለሞያ ገለጻ እንደተሰጠ ነው የተገለጸው፡፡

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች በመድረኩ ሊወሠኑ እንደማይገባ የገለጹ ሲሆን፤ ምርጫው እንደመቅረቡ መጠን መሠል መድረኮች በተከታታይ እንደሚዘጋጁ ቃል መግባታቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.