Fana: At a Speed of Life!

የጤናማ እናትነት ወር በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤናማ እናትነት ወር እናት የቤተሰብና የሀገር ምሰሶ ናት በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው።

ወሩ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልል አመራሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ነው እየተከበረ ያለው።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በተገቢው ሰዓትና ቦታ በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ቢሰጥ የአብዛኛውን የእናቶች ሞት መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የእናቶችንና የህፃናትን ጤና በማሻሻል ብሎም በመጠበቅ ረገድ በተለይም እናቶች መከላከል በሚቻሉ ምክንያቶች የሚደርስባቸውን ህመምና ሞት ለመታደግ የተሰሩ ስራዎችን በማየት ጠንካራውን ማስቀጠልና ጉድለት የታየበትን ማስተካከል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለ30 ቀናት በሚቆየው የጤናማ እናትነት ወር በወሊድ እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.