Fana: At a Speed of Life!

“በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ውስጥ የህግ የበላይነትና የዜግነት ክብር ይዞታ” በሚል ርእስ የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)“በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ውስጥ የህግ የበላይነትና የዜግነት ክብር ይዞታ” በሚል ርእስ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱ በፖሊሲ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች መካከል ውይይት በማካሄድ በለውጡ ሂደት በሕግ የበላይነትና በዜግነት ክብር የሃሳብ ልዕልና ለማዳበር ያለመ ነው ተብሏል።

የፓናል ውይይቱን  ሚኒስቴሩ  ከደህንነት ጥናት ተቋም ጋር በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተመላክቷል።

የሰላም ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሰይድ በመክፈቻ ንግግራቸው ÷ ፓናል ውይይቱ የሰላም ሚኒስቴር በህግ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል አንዱ የሆነውን ዜጋ ተኮር የህግ የበላይነትና ዴሞክራሲን ለማስረጽ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች ውስጥ ዋነኛው ነው ብለዋል።

በሚኒስቴሩ የዴሞክራሲና የዜግነት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር ሞገስ ደምሴ ÷‘የህግ የበላይነትና የዴሞክራሲ ግንባታ በኢትዮጵያ’ በሚል ርእስ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በወቅቱም የውይይቱ  ተሳታፊዎች ህግ የሚወጣ ቢሆንም ትግበራ ላይ ሰፊ ክፍተት እንዳለ ተናግረዋል ።

አያይዘውም  ዜጎች ፍርድ ቤቶች ላይ መተማመን እንደሌላቸውና እንግልት የሚበዛባቸው ተቋማት ተደርገው እንደሚታዩ ጠቁመው÷ ችግሮቹን ለመቅረፍ ግልጽ ውይይትቶች በማረግ አስፈላጊ የማስተካከያ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ  ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.