Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሰራዊት  በከፈለው መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከብተና ያዳነ እና አሁን ለተደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን የክልል ርዕሳነ መሰተዳድሮች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መከላከያ ሰራዊት  በከፈለው መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከብተና ያዳነ እና አሁን ለተደረሰበት ሰላም፣ልማትና  ከፍተኛ ሚና መጫወቱን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድና የአማራ ክልል  ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

የሶማሌ ክልል ባለፋት በርካታ አመታት በከፍተኛ የፀጥታ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አመራርና አባላት ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግርን በፍጥነት በመቆጣጠር ህዝባዊነቱን ያስመሰከረ ሲሆን በዚህም ክልሉ ላይ ይደርስ የነበረውን ኪሳራ መቀነስ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሃት ጁንታ ኢትየጵያን ለመበተን አስቦ በሰራዊቱ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ቢሰነዝርበትም የህዝብ ልጅ የሆነው ሰራዊት ከደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት በፍጥነት አገግሞ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት በሁለት ሳምንት ውስጥ ጁንታውን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ከከተጋረጠባት  አደጋ አድኗል ብለዋል።

አቶ ሙስጠፌ  የህወሃት ርዝራዦች ቀደም ሲል የዘረጉትን የሴራ ኔትወርክ በመጠቀም ሰራዊቱ ላይ ያልተገባና ከእውነት የራቀ ውሸት እያስተጋቡ ቢሆንም ሰራዊቱ ግን በህዝባዊነቱ ስነ ምግባር ተመራጭ በመሆን የጎረቤት ሃገራትን ጭምር በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቀ የሚገኝ ተወዳጅ ሰራዊት ነው ብለዋል።

በተያያዘ የመከላከያ ሰራዊት በከፈለው መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከብተና ያዳነ ሀይል ነው  ሲሉ የአማራ ክልል  ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል፡፡

 

ሰራዊቱ በህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው የፈፀመው ግዳጅ ህዝቡ ለሰራዊቱ የነበረውን የተዛባ አተያይ ያከመበት ነውም ብለዋር አቶ አገኘው።

የህወሀት ሀይሎች በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ይከሰቱ የነበሩ ዘርና ብሄር-ተኮር ግጭቶችን ከመወጠን ጀምሮ የእኩይ አላማቸው ፈፃሚ የሆኑ ሀይሎችን በመመልመል ፣ በማሰልጠንና በማሰማራት የህዝቦችን አብሮነታዊ ሰላምና ማንነታዊ አንድነት ሲያደፈርሱ ኖረዋል ብለዋል።

በህልውና ዘመቻው መላው የአማራ ክልል ህዝብ ፣ ባለሀብቶች ፣ የህክምና ባለሙያዎች እና በየከተሞቹ የሚገኙ እናቶች የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ልክ እንደ ከሃዲ ጁንታዎች ሁሉ አሁን ላይ የሌላ ሀይል ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑትን የሱዳን ተንኳሽ ሀይሎችን ጨምሮ እየታዩ ካሉ አገራዊና ከባቢያዊ አዝማሚያዎች አንፃር እንደ አገር ህብረታችንን አጠንክረን ከሰራዊታችን ጎን የምንቆምበትን በር የሚከፍትልን ነው።

የአማራ ክልል ህዝብና መንግስትም በየትኛውም መልኩ በሚያስፈልጉ ድጋፎች ሁሉ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆሙ ርዕሰመስተዳድሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.