Fana: At a Speed of Life!

በጭላሎ ጋለማ ደን የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርሲ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አካል የሆነው የጭላሎ ጋለማ ደን የእሳት ቃጠሎ አደጋ  መከሰቱ ተገለጸ፡፡

ፓርኩ ከሚያካልላቸው ዘጠን ወረዳዎች ውስጥ በሰባቱ የእሳት አደጋ የተከሰተ ሲሆን÷ ረጅም ጊዜ ያስቀጠሩ የደን ዝርያዎች ጉዳት  እንደደረሰባቸውም ነው የተመላከተው፡፡

የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ሃላፊ አቶ ሙሀመድ ቲፎ÷የደረሰዉን እሳት አደጋ ለመቆጣጠር በተወሰነ ህዝብ ተሳትፎ ጥረት መደረጉን  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋው አምስት ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን÷ ዛሬ ላይ  ግን ይበልጥ ተባብሶ ቀጥሏል ነው የተባለው፡፡

የተለያዩ ህፅዋቶችና እንስሳቶችን የያዘዉ ጭላሎ ተራራ በየግዜዉ በተለያዩ ምክንያቶች በእሳት አደጋ እተፈተነ  መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በደኑ ላይ ከሰሞኑ የተከሰተው  ይህ የእሳት አደጋ መንስኤው ለግጦሽና በግጦሽ ላይ የሚገኙ የቤት እንስሳትን የዱር እንስሳት  እንዳያጠቁ በሚል የተለኮሰ ስለመሆኑ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ከእሳት አደጋው ጋር በተያያዘ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።

በደኑ ላይ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ህብረተሰቡ ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እንዲያዝ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በስንታየሁ አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.