Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለምርመራ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለምርመራ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገለት፡፡

ድጋፉ በተባበሩት መንግስታት የአደንዛዥ እፅና ሌሎች ወንጀሎች ጽህፈት ቤት የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር  ፕሮግራም የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

የጽህፈት ቤቱ ዋነኛ ተልዕኮም  በዓለም አቀፍ ደረጃ አደንዛዥ እፅ ፣ሙስና፣ ሽብርተኝነትና ሌሎች ወንጀሎችን በመከላከል ለሰላምና ደህንነት ፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር እና ለልማት አስተዋፅዖ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም  የተለያዩ ኮምፒውተሮች፣ የፎረንሲክ መመርመሪያ መሳሪያዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን ድጋፍ አደርጓል፡፡

ድጋፍ የተደረጉት ቁሳቁሶችም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮው ለሚሰራቸው የምርመራ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ ÷ በድርጅቱ የተደረገው ድጋፍ ለወንጀል ምርመራ ስራዎች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው÷ በራሳቸውና በቢሮው ስም ከፍተኛ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.