Fana: At a Speed of Life!

የካናዳ-አፍሪካ “ከአየር ብክለት የፀዳ ልማት” አውደጥናት በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳ-አፍሪካ “ከአየር ብክለት የፀዳ ልማት” አውደጥናት በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው።

በዚህ መድረክ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር  አህመዲን መሀመድ ÷በኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታን ለመፍጠር እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል የማዛወር ሂደት፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ህግ ክለሳ፣ የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ስራዎች እንደተሰሩና ወደ የዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ለመግባት መደላድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል።

የስታርትአፕ አዋጅ፣ የብሔራዊ የፈጠራ ስራ ፈንድ መቋቋም፣ ከባንኮች በቀላሉ ብድር ማግኘት እና የሥራ ፈጣሪዎች የውጭ ምንዛሬ የባንክ ሂሳብ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪዎች ኢትዮጵያ ተመራጭ እንድትሆን ያስችላታልም ነው ያሉት።

ሚኒስትር ዴኤታው ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር፣ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ ገበያን ማስፋትና የኮቪድ 19 ጫናዎችን ለመቀነስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

እየተሰሩ ባሉ የማሻሻያ ስራዎች ለቴክኖሎጂ የስራ ፈጣሪዎች መጪው ጊዜ በኢትዮጵያ ብሩህ እንደሚሆን ተገልጿል።

በካናዳና፣ ሴኔጋልና ኢትዮጵያ በጋራ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት   እየተካሄደ ያለው አውደ ጥናቱ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ፈጠራ የታከለበት  የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የሚቻልባቸውን መንገዶች የሚፈትሽ ነው መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.