Fana: At a Speed of Life!

በሎስ አንጀለስና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሎስ አንጀለስ እና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በመደገፍ እና የአሜሪካ መንግስት አካላት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና በመቃወም በኮንግረስ አባል ካረን ባስ የሎስ አንጀለስ ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ የአሜሪካ ኮንግረስ የካሊፎርኒያ ተመራጭ የሆኑትና በኮንግረሱ የአፍሪካ፣ የዓለም ጤና ድርጅት፣ የሰብዓዊ መብቶች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን የሚከታተለው ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ካረን ባስ በቅርቡ በኮንግረስ ያቀረቡት ኢትዮጵያን የተመለከተ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ሚዛናዊነት የጎደለው እና በተጨባጭ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ ውድቅ እንዲደረግ እና የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ በሚያንፀባርቅ መልኩ እንዲዘጋጅ በመጠየቅ ያወጡትን መግለጫ ቅጂ ለፅህፈት ቤቱ አስገብተዋል።

ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያን በተመለከተ በተለያዩ የአሜሪካ የመንግስት አካላት እየወጡ ያሉ የተዛቡ መረጃዎችን የሚቃወሙ፣ የአሜሪካ መንግስት ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚጠይቁ እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚታየውን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.