Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ለ770 ሺህ ሰዎች የሚያደርገውን የምግብ ድጋፍ ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ እያቀረበ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ ያደርግ የነበረውን የምግብ ድጋፍ በማሳደግ ለ770 ሺህ ሰዎች ምግብ ነክ ድጋፍ ለማድረግ የያዘውን እቅድም በትናንትናው እለት በይፋ ጀምሯል፡፡

በዚህም በትናንትናው እለት ለ18 ሺህ የእደጋ ሃሙስ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ ሩዝ፣ በቆሎ እና የአትክልት ዘይትን ያካተተ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ጋር በተያያዘ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ተቋሙም የድጋፉን ተደራሽነት ለማጠናከርና ለማሳደግ እንደሚሰራ መግለጹም ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.