Fana: At a Speed of Life!

ኦነግ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ።

ለሁለት ቀናት አጠቃላይ ጉባዔውን ያካሄደው ፓርቲው አዲስ ሊቀመንበርም መርጧል።

ፓርቲው ባደረገው ጉባኤ አቶ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ብርሃኑ ለማ እና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል።

ጉባዔው 43 ቋሚ እና 5 ተለዋጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል።

በጠቅላላ ጉባኤው ህገ ደንቡን ያሻሻለው ፓርቲው የስነ ስርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴም አቋቁሟል።

ፓርቲው እራሱን ከምርጫ ማግለል እንደማይፈልግ የገለጸ ሲሆን የዕጩዎች መዝገባ ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ ግን ምርጫ ቦርድ ከፈቀደ ወደ ምርጫው እንደሚገቡም አስረድተዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.