Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወቅቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተዘጋጀ ነው – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ለማሻሻልና የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ ወደ ተግባር ለማስገባት አውደ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል።

አውደ ጥናቱ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን በማሳተፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

መድረኩ ቀደም ሲል የተሰበሰቡ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግ አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ለማሻሻልና የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ ነው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ተወካይ ዳይሬክተር ወይዘሮ ዛፏ አብርሃ የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያው ባለፉት ጊዜያት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል የነበሩትን የስርዓተ ትምህርት ችግሮችን ሊቀርፍ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሥርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት የይዘት ፍሰቱ፣ ተፈላጊ የመማር ብቃት መለኪያና ሰነዶች በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ያሉ የብቃት ማረጋጋጫ ተቋማት ተሞክሮዎችን በመውሰድ የተገመገመ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዝግጅቱ በሂደት ላይ ያለው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ እንዲሆን የግብረገብ ትምህርትን ያካተተ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ለተማረ ዜጋ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

በሥርዓተ ትምህርቱ አዘገጃጀት ሂደት በቋንቋ፣ በሂሳብ፣ በሳይንስና በማህበራዊ ትምህርት ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በአውደ ጥናቱ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከአምስቱ ከፍተኛ ትምህርት የልህቀት ማዕከላት የተውጣጡ የዘርፉ ምዑራን፣ ባለሙያዎችና የሲቪል ማህበራት ተሳታፊ ሆነዋል።

ለአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ከተጠናቀቀ በኋላ ለትግበራ ወደ ክልሎች እንደሚላክ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላከታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.