Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ከዕጩዎች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ከ500 በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዕጩዎች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ከ500 በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በምርጫ ሂደት ዙሪያ ተወያይቷል፡፡

በዚህ ወቅትም በሁለት ዙር በተደረገው የዕጩዎች ምዝገባ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገባቸውን አስታውቋል፡፡

የመጨረሻው ቁጥር ተጣርቶ የሚቀርብ ቢሆንም 8 ሺህ 209 ዕጩዎች መመዝገባቸውም ታውቋል።

በፓርቲዎች በኩል የተለያዩ ቅሬታዎች የቀረቡ ሲሆን፥ የምርጫ ቢሮ ክፍት አለመሆን፣ ተጨማሪ መረጃዎችን በምርጫ ክልል አስፈፃሚዎች መጠየቅ (የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የፍርድ ቤት ደብዳቤ) ተጠቅሰዋል፡፡

ቦርዱ የቀረቡትን አብዛኛዎቹን አቤቱታዎች የፈታ ሲሆን ከአባላት መታሰር እና ከቢሮ መዘጋት ጋር ተያይዞ የተነሱ ጥያቄዎችን በቦርዱ አቅም መፍታት አልተቻለም ተብሏል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.