Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የኢትዮ ቻይና የፖለቲካ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የኢትዮ ቻይና የፖለቲካ ውይይት በሚኒስትር ዲኤታዎች ደረጃ ተካሄደ።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ውይይት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ሊ ተሳትፈዋል።

ቻይና ወሳኝ የኢትዮጵያ ወዳጅ ናት ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሀገራቱ በፖለቲካ፣ ንግድ ፣ ኢኮኖሚ እና በሰብዓዊ ጉዳዮች ጥብቅ ግንኙነት አላቸው ብለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ቻይና በኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረጓ ምስጋና አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በመሰረተ ልማት፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እና በቴክኒካዊ ትብብር ቻይና ላደረገችው አስተዋፅኦ ሚኒስትሩ አመስግነዋል።

የቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያና ቻይና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ ትብብር እንዳላቸውና በቅርብ ጊዜያትም በከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደረጃ ግንኙነት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ ሀገራቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ውጤታማ ትብብር ማድረጋቸውን በውይይቱ ወቅት ገልፀዋል።

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በሁለትዮሽና በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትስስር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላትም ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅት በትግራይ ክልል ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ችግር ዙሪያ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.