Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሃይል ዘርፍ የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት እየሰራች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ብሄራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ቀርጻ እየሰራች መሆኗን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ በበይነ መረብ በተካሄደው የበርሊኑ የኢርነጂ ሽግግር ውይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱ “ዓለም አቀፍ ዘላቂ የልማት ግቦችን እንደየአካባቢውና በየደረጃው እንዴት መተግበተር ይቻላል?” በሚለው ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የኃይል አቅርቦትንና ተደራሽነትን ማሳደግ ለሁሉም ዘመናዊ ሕይወት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት አብዛኛው የኃይል ምንጭ ማገዶ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ የኃይል ተደራሽነትን ማስፋት በተለይ በሴቶችና ህጻናት ጤና ላይ የሚያርፈውን ጫና በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት ንጹህና ታዳሽ ሃይል በማልማት ላይ እንደሆነች እንዲሁም የኃይል አቅርቦቱን በሚፈለገው ልክ ተደራሽ ለማድረግ በራሷ አቅም ገንዘብ ከማሰባሰብ በተጨማሪ ተቋማዊ እንዲሁም የፖሊሲ ማሻሻያዎችንና ሪፎርሞችን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.