Fana: At a Speed of Life!

ኢኖቬሽንን ለልማት የተሰኘ ዓለም ዓቀፍ ፕሮጀክት በይፋ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢኖቬሽንን ለልማት የተሰኘ ዓለም ዓቀፍ ፕሮጀክት በይፋ ስራ መጀመሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢኖቬሽን ለልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የቦርድ ስብሰባ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር ፣ በኢትየጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብር ኤጀንሲ እንዲሁም ሌሎች የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በበይነ መረብ ተካሄዷል፡፡

ፕሮጀክቱ ሀገር አቀፍ የኢኖቬሽን እና ኢንተርፕርነርሺፕ ከባቢያዊ ሁኔታን ማጠናከር፣ የስራ ዕድል መፍጠር እና ምርትና ምርታማነትን በማሳግ ለኢኮኖሚው እድገት አስተዋጽኦ የማድረግ ዓላማ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሴቶች እና ወጣቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.