Fana: At a Speed of Life!

በላስቬጋስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንዳንድ የአሜሪካ አካላት የሚደረገውን ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫናን በመቃወም ሰልፍ አካሂዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በላስቬጋስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንዳንድ የአሜሪካ የህግ አውጪ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት የሚደረገውን ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫናን በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባደረጉት ሰልፍ የህወሓት ቡድን በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈፀም ያደረሰውን የሰላም መደፍረስ እና የክህደት ወንጀል አውግዘዋል፡፡

እንዲሁም የክህደት ወንጀል በማውገዝ እና በሕወሓት ስርዓት ተጠቃሚ በሆኑ አንዳንድ የዳያስፖራ ቡድኖች አባላት ግፊት በኢትዮጵያ ላይ በአንዳንድ የአሜሪካ የህግ አውጪ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት የሚደረገውን ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ተቃውመዋል፡፡

ሰልፉን ያስተባበሩት በላስ ቬጋስ የኢትዮጵያ ኮሚዩቲየ እና የላስ ቬጋስ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ንዑስ ቡድን አባላት ናቸው።

የዳያስፖራ አባላቱ ለሀገራቸው እና ለመንግስት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

በዲፕሎማሲው ረገድ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ኢ-ፍትሃዊ  ጫና በተደራጀ መንገድ ለመቋቋም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለመታገል መወሰናቸውንም አረጋግጠዋል።

ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያንፀባርቅ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በሰልፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጁንታው ቡድን እና ተባባሪዎቹ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈፀሙትን አሰቃቂ ወንጀሎች በማውገዝ፣ አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በጥንቃቄ በመመርመር ትክክለኛ ውሳኔ እንዲሰጥ ጥሪ የሚያቀርቡ እና ሌሎችም ወቅታዊ መፈክሮችንም በሰልፉ ላይ አሰምተዋል።

በመጨረሻም ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸውን በኔቫዳ ግዛት ተመራጭ ለሆኑ ሁለት ሴናተሮች እና አራት የኮንግረስ አባላት በፅሁፍ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.