Fana: At a Speed of Life!

ባልደራስ እና አብን የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ፓርቲዎቹ የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው ለመስራት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያን ከፅንፈኛ ሀይሎችና አስተሳሰቦች መታደግ የሚያስችል ዓላማ ይዘው ጥምረት መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነትም ተፈራርመዋል።

ፓርቲዎቹ መላ ኢትዮጵያውያን በእኩልነት፣ በወንድማማችነት፣ በፍትህና በሰላም የሚተዳደሩበትን ዘላቂ ስርአት ለማስፈን የትግል እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ በስምምነቱ ላይ አንስተዋል፡፡

ትብብሩ በቀጣይ በሃገሪቱ እንዲፈጠርና እንዲጎለብት የሚፈለገውን ሃገራዊ በጎ ሀይሎች ጥምረት መሰረት እንዲሆን ያለመ መሆኑም ፓርቲዎቹ ገልዋል፡፡

በመጭው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫም የመራጮችን የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት ፓርቲዎቹ በጋራ ለመስራት በማሰብ የመሰረቱት የፖለቲካ ትብብር መሆኑንም ነው የገለፁት።

በሃገሪቱም ሆነ በዜጎች ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እንዳሉ የገለጹት ፓርቲዎቹ፥ ይህንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር ለመታገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና ትብብሩ ከምርጫው በኋላም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.