Fana: At a Speed of Life!

30 ሰዎች በህገ – ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ 30 ሰዎች በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
መነሻውን ከጎንደር ከተማ ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብራሃጅራ ከተማ ባደረገ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሸራ በማልበስ ወደ አብራጅራ በኩል የሳንጃ ኬላን ለማለፍ ሲሞከር በተደረገ ጥቆማ መያዛቸው ታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም አሽከርካሪው እና ግለሰቦቹ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡
ህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችን ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ወደ ህግ ማቅረብ እንደሚገባ መገለጹን ከታች አርማጭሆ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.