Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዋሽንግተን የሚገኙ አምባሳደሯን ጠራች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ሩሲያ በዋሽንግተን የሚገኙ አምባሳደሯን ጠራች፡፡

የአሜሪካ ብሄራዊ የመረጃ ተቋም ሩሲያ በ2020 በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ለደጋፊዎቻቸው የቅስቀሳ ዘመቻ ሲያደርጉ እንደነበር የሚያሳይ ባለ 15 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከኤቢሲ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ፑቲን ለዚህ ድርጊታቸው ዋጋ ይከፍላሉ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሩሲያም አስተያየቱን ተከትሎ አምባሳደሯን መጥራቷ ተሰምቷል፡፡

የአምባሳደሩ ጥሪ በሃገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ማይመለስ ዲፕሎማሲያው ችግር ከመግባቱ በፊት ለመመካከር ያለመ መሆኑን ከሩሲያ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በተጨማሪም ሩሲያ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች ተብሎ የሚቀርብባትን ክስ መሰረት አልባ ነው በሚል ውድቅ አድርጋዋለች፡፡

አሜሪካ በአንጻሩ የሪፖርቱ ማጠቃለያ ተከትሎ በመጪዎቹ ሳምንታት ማዕቀብ ትጥላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.