Fana: At a Speed of Life!

50 ሚሊየን የአፍሪካ ሴቶች ይናገሩ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 ሚሊየን የአፍሪካ ሴቶች ይናገሩ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ከፕሬዚዳንቷ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የኮሜሳ አባል ሃገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በዋናነት ሴት የአፍሪካ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ያልሆኑ መረጃዎችን እንዲያገኙ በማድረግ በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማስቻል የታሰበ መሆኑን ከሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.