Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የጃፓንን የንግድ ግንኙነት ለማሻሻል በሚረዱ መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኒቶ ታካኮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው የኢትዮጵያ እና የጃፓን የንግድ ግንኙነት እና በማምረቻው ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማሻሻል በሚረዱ መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በውይይቱ አቶ መላኩ ጃፓን እና ኢትዮጵያ ታሪካዊ ዲፕሎማሲ እና የንግድ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡
የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚችሉባቸውን ዕድሎችም አብራርተዋል፡፡
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት፣ በአቅም ግንባታ ፣ በስልጠና እና በቴክኖሎጂ ድጋፍ ለመስጠት ሃገራቸው ያላትን ፍላጎት አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.