Fana: At a Speed of Life!

ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና ፌስቡክ በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይት ፕሮግራምን አስጀመሩ 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና ፌስቡክ የቱሪዝም ዘርፉ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲያገግም የሚያግዝ የዲጂታል ግብይት ፕሮግራምን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ፕሮግራሙ በትብብር የሚሰራ ሲሆን በሃገር በቀሉ ሰመር ሚዲያ እንደሚተገበር ተገልጿል፡፡

በዋናነትም በኮቪድ 19 የተጎዳውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማገዝ የሚተገበር መሆኑ ተነስቷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፈው አመት ነሐሴ ወር ላይ በአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የተሰማሩ አካላትን ማገዝ አላማው ያደረገ የሙከራ ፕሮግራም ተተግብሯልም ነው የተባለው፡፡

በዋናነትም በአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የተሰማሩ አካላት ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን በመጠቀም፥ የቀጥታ (ኦንላይን)  የንግድ ግብይትን ማሳደግ የሚችሉበትን ልምድ እንዲያገኙ ማስቻልን አላማው ያደረገ ነበር ነው የተባለው፡፡

በቱሪዝም ኢትዮጵያ እና ፌስ ቡክ የተጀመረው ፕሮግራምም የቀጥታ ግብይትን ለማሳደግና በኮቪድ19 ምክንያት የተጎዳውን ዘርፍ በማነቃቃት የዘርፉን ተዋናዮች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.