Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ19 መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ መተግበር በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የኮቪድ መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ነው የተወያዩት፡፡

ውይይቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘውን የኮቪድ19 ወረርሽኝን በተመለከተ ከተጋረጠው ስጋት ለመውጣትና ህዝቡን ለመታደግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በሳምንቱ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ኮቪድ 19 በማህበረሰቡ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመዛመት ላይ እንደሚገኝ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ወደ ኮቪድ19 የህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ግለሰቦች ውስጥም 69 የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑም አስታውቋል፡፡

ኢንስቲቲዩት ይፋ ባደረገው መረጃ ከየካቲት ስድስት በፊት ባሉት ሰባት ቀናት ከ100 ግለሰቦች ውስጥ በአማካኝ 19 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.