Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በቀጣይ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ ምክክር አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በቀጣይ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ በአውሮፓውያኑ ከ2ዐ21- እስከ 2ዐ27 ድረስ ኢትዮጵያና ህብረቱ ስለሚኖራቸው ትብብር አስመልክቶ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ መሆኑ ተመላክቷል።

በውይይቱ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስቴር፣የተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ናቸው፡፡

ውይይቱም ያተኮረው የኢትዮጵያን የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ እና የአውሮፓ ህብረት የልማት ፖሊሲን በረቂቅ ሰነዱ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ ላይ ነው ተብሏል፡፡

የምክክር መድረኩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ  ያስሚን ወሀብረቢ÷ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የረጅም ጊዜ ጠንካራና ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ የመጣ ትብብር ያላቸው መሆናቸውን በማስታወስ እስከአሁን ህብረቱ ለሚያደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተለይም በጤና፣በአየር ንብረት ለውጥ፣በምርጫ ድጋፍ፣በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር እና በግብርና መስክ ህብረቱ ባደረገው ድጋፍ በርካታ አመርቂ ውጤቶች እንደተገኙ ሚኒስትር ዴኤታዋ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በድህረ ኮቶኑ ስምምነት መሰረት ከህብረቱ የተለያዩ የልማት ድጋፎች ከሚያገኙ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ አገሮች በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ የመልካም ግንኙነት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተነሱት ሀሳቦች በረቂቅ የትብብር ሰነዱ ላይ ተካተው በአውሮፓውያኑ  ከግንቦት 2ዐ21 በፊት ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.