Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በትግራይ ክልል ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 52 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በትግራይ ክልል ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 52 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ዘመቻው ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

የአሁኑ ድጋፍ ለ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች እና የህግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ 62 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ያስችላል ተብሏል፡፡

በዚህም ህይወት አድን ድጋፍ፣ መጠለያ፣ አስፈላጊ የጤና ክብካቤ፣ አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት እና የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ባለፈም በህግ ማስከበር ዘመቻው የተለያዩ ቤተሰቦችን ለማገናኘት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 153 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.