Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚሞክሩ ሀይሎችን በማውገዝ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በመደገፍና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማደናገር በኢትዮጵያ ላይ ህጋዊ ያልሆነ ጫና ለማድረግ የሚሞክሩ ሀይሎችን በማውገዝ በካንቤራ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
ሰልፈኞቹ መንግስት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ህግ ለማስከበር የወሰደውን እርምጃ እንደሚደግፉ፣ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት የሚሰሩ አካላትን እንደሚቃወሙ ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ምዕራባውያን ሃገራት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና አንድነቷን ለማስቀጠል የምትወስደውን እርምጃ ከመደገፍ ባሻገር በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ መግባት የሌለባቸው መሆኑን የሚያሳዩ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን መካከል ትብብርና ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.