Fana: At a Speed of Life!

ሳሚያ ሱሉሁ ዛሬ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ  ፈጸሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የሀገሪቱ ስድስተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ዛሬ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ማጉፉሊ በ61 ዓመታቸው ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት ነው።

የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓቱ  ዛሬ ዳሬሰላም በሚገኘው ቤተመንግስት መከናወኑን የመንግስት ቃል አቀባይ ተናግረዋል ፡፡

ሳሚያ ሱሉሁ በታንዛኒያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡

የ61 ዓመቷ ሳሚያ ሱሉሁ በሕገ-መንግስቱ መሠረት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የማጉፉሊ ቀሪ የስልጣን ዘመን እስከሆነው 2025 ድረስ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ ተገልጿል ፡፡

ከዚህ ባለፈም ቅዳሜ እለት የፓርቲያቸው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን፥ በስብሰባው አዲስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደሚመረጥ ይጠበቃል፡፡

የቀድሞዋ የቢሮ ጸሐፊ እና የልማት ሠራተኛ ወይዘሮ ሱሉሁ የፖለቲካ ህይወታቸውን በፈረንጆቹ 2000  ከፊል የራስ ገዝ በሆነችው ዛንዚባር መጀመራቸው ይነገራል።

ምንጭ፡-ኔሽን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.