Fana: At a Speed of Life!

የሞዛምቢክ አየር መንገድ ወደ ኬንያ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሞዛምቢክ አየር መንገድ ወደ ኬንያ የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው ማቋረጡን አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ ከኬንያ ወደ ሞዛምቢክ እንዲሁም ከሞዛምቢክ ወደ ኬንያ የሚደረገውን በረራ ማቋረጡን ነው ያስታወቀው፡፡
ይህ ውሳኔም በአሰራር ምክንያት የተላለፈ መሆኑም ተነግሯል ፡፡
አየር መንገዱ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጥም ውሳኔው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከአየር ትራንስፖርት መቀዛቀዝ ጋር የተቆራኘ ነው ተብሎ ይታሰባል ፡፡
ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ በወረርሽኙ ምክንያት የተወሰነ የሃገር ውስጥ በረራዎችን መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.