Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በካናዳ -አፍሪካ የአረንጓዴ ልማት ስብሰባ ላይ ተሳተፈች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ  በካናዳ -አፍሪካ የአረንጓዴ ልማት ስብሰባ ላይ ተሳትፋለች።

በአነስተኛ  የካርበን ልቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም  የልማት ስትራቴጅን ለመከተል  ካናዳ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ተባብራ መሥራት የምትችልባቸውን  አማራጭ የሚያፈላልግ ስብሰባ ለሶስት ቀናት በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡

በስብሰባው ላይ  የፕላንና ልማት ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የኢትዮጵያን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጅ ለተሳታፊዎቹ  አቅርበዋል፡፡

በዚህም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመከላከል በየዓመቱ የችግኝ ተከላ እያካሄደች መሆኑን ጠቅሰው÷ በአፍሪካ እየተስፋፋ ያለውን በረሃማነትን ለመግታት እና ባደጉ ሃገራት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ለመቋቋም  እንደ ካናዳ ያሉ ያደጉ ሃገራት  በቴክኖሎጅና በገንዘብ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ያለውን የቢዝነስ ዕድሎች የሚያስተዋውቅ መድረክ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ልዩ አማካሪ ዶክተር እውነቱ ሃይሉ በሀገሪቱ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና ሃገር በቀል ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጅ ላይ  ማብራሪያ  በመስጠት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በስብሰባው ኢትዮጵያ በሁሉም ሴክተሮች ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከአረንጓዴ ልማት አኳያ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የካናዳ ዓለም አቀፍ ሚኒስትር ካርና ጉድ 132 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የካናዳ – አፍሪካ ልማት ባንክ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ለማበርከት ቃልመግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.