Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስምንት ወራት 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 8 ወራት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች  መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በ2013 በጀት ዓመት ስምንት ወራት በተሠራው ጠንካራ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ሥራ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡

ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ስምንት ወራት አፈጻፀም ጋር ሲነጻፀር  720 ሚሊየን 298 ሺህ 971 ወይንም በ47 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ዕውቀት፣ ጉልበት ፣ ህይወት በመሰዋትና አካልን በመገበር ጭምር ሊያዙ መቻሉን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.