Fana: At a Speed of Life!

በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት የኢንቨስትመንት ፎረም አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል የቢዝነስ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ የቢዝነስ ፎረም በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት በበይነ መረብ አካሂዷል፡፡
በፎረሙ የ108 የኩባንያ ተወካዮች እና የንግድ ምክር ቤት አባላቶች ተሳተፈዋል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አባቢ ደምሴ እና በሎስ አንጀለስ ቆንስላ ጄኔራል አምባሳደር ሙሉጌታ ከልል ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የስራ ኃላፊዎቹ በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት አመቺ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑ የአሜሪካ ባለሃብቶች በመረጡት ዘርፍ እንዲሰማሩ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንደሚደርጉላቸው በማረጋገጥ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ቅበላ አቅም እና ለባለሃብቶች የተመቻቹ ሁኔታዎች ላይ ተሳታፊዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የማዕድን እና ፔትሮሊየም ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም ተጨማሪ ገለፃ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.