Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በጸጥታና ህግ ማስከበር  ስራ ላይ ስልጠና የወሰዱ 610 አባላትን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጸጥታና ህግ ማስከበር  ቀጠና አንድ የስራ ላይ ስልጠና የወሰዱ 610  አባላትን አስመርቋል።

ዛሬ የተመረቁት አባላት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት ከአንድ ወር በላይ የስራ ላይ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተመላክቷል።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው የአድማ ብተና ስልጠና ፣የአካል ብቃትና ወታደራዊ ሰልፍ ስልጠና እንደወሰዱ የቀጠና አንድ ምክትል አዛዥ ኮማንደር አብዲሳ ባይሳ ገልጸዋል።

በስራ ላይ የሚሰጥ ስልጠና ቀልጣፋ ስራ ለመስራት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም  ነው የገለጹት።

አያይዘውም እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎችን በዘላቂነት ለመስጠት የሎጀስቲክ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.