Fana: At a Speed of Life!

ጆ ባይደን ቭላድሚር ፑቲንን ገዳይ ማለታቸው ተቀባይነት የለውም- ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስለ ቭላድሚር ፑቲን የሰጡት አስተያየት ተቀባይነት የለውም ሲሉ ገለፁ።

ጆ ባይደን ቭላድሚር ፑቲንን ገዳይ ማለታቸው ተቀባይነት የሌለውና  ከፕሬዚዳንት የማይጠበቅ አስተያየት ነው ሲሉ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

ባለፈው ረቡዕ ከኤቢሲ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፑቲን ገዳይ መሆኑን ያምናሉ ተብለው የተጠየቁት ፕሬዚዳንቱ አዎ አምናለሁ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ፑቲን ለጆ ባይደን በሰጡት ምላሽም “ይህንን ያለ ነው ተግባሩን የሚፈፅመው ብለዋል።

ቱርክ እና አሜሪካ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ቢሆኑም ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን  ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ የስልክ ውይይት አላደረጉም።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.