Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ በአየር ሰዓት ድልድል ዙሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእጩ ምዝገባን መጠናቀቅ ተከትሎ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጠው የአየር ሰዓት ድልድል ሂደት ላይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ ላይ ባለስልጣኑ ለአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድሉ  ያከናወናቸውን መሰረታዊ የአውቶሜሽን ስራዎችን እንዲሁም የቀሩ ሂደቶችን ለቦርዱ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለአየር ሰዓትና ለጋዜጣ አምድ ድልድሉ የተዘጋጀውን የእጣ ማውጫ ሶፍትዌር የገመገሙ ሲሆን ስራው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ ተደራጅተው  ለባለስልጣኑ እንደሚላኩ  ገልፀዋል።

ባለስልጣኑም ለጋዜጣ አምድና ለአየር ሰዓት ድልድል መሰረታዊ ግብዓቶች ተሟልተው እንደቀረቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን እንደሚያጠናቅቅ መገለፁን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአየር ሰዓት እጣ አወጣጥ ስርዓቱንም በተመለተ የቦርዱ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እንደሚያከናወን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.