Fana: At a Speed of Life!

በ8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የጊንጪ ሃይል ማከፋፈያ ዛሬ ይመረቃል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የጊንጪ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ ይመረቃል።
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በሚገኙበት ይከናወናል።

ኤ ዲ ዲ ኤም እና ጂ የተሰኘው ፕሮጀክት አካል የሆነው የጊንጪ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 230/15 ኪሎ ቮልት ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፈርመሮች ተገጥመውለታል።

የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያው እስከ 100 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ሲኖረው አስር ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮችም አሉት።

ግንባታውን ላርሰን ኤንድ ቱርቦ የተሰኘ የሕንድ ኩባንያ ያከናወነው ሲሆን፥ ኤም ቪ ቪ ዲከን የተባሉ የጀርመንና ስዊዘርላንድ ኩባንያዎች የማማከር ሥራውን ሰርተዋል።

የጊንጪ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለጊንጪ ከተማና ለአካባቢው አስተማማኝ ሃይል ማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የግንባታው ወጪም 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት ቀሪው 85 በመቶ ደግሞ ከፈረንሳይ የልማት ባንክ በተገኘ ብድር የተሸፈነ ነው፡፡

በቅድስት ተስፋዬ እና ታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.