Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ሶስት ወረዳዎች ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሶስት ወረዳዎች ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋድቤል ሙን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአቦቦ ወረዳ ለአንድ ሠዓት ያህል ያለማቋረጥ ንፋስ ቀላቀሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በአምስት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ከ180 በላይ የመኖሪያ ቤቶችና የመንግስት ተቋማትም ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ከአቦቦ ወረዳ በተጨማሪ በጋምቤላና ኢታንግ ልዩ ወረዳዎችም ተመሳሳይ ጉዳት መድረሱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ግብረ ሃይል ተደራጅቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በወረዳው በደረሰው አደጋ ከ1 ሺህ 360 በላይ ቤተሰቦች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፤ ሰሞኑን የጣለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በነዋሪዎች ቤትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የክልሉ መንግስት የተጎጂዎችን ዝርዝር መሰረት በማድረግም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያቀርብም ተናግረዋል።

የክልሉ ካቤኒ ለተጎጂዎች ድጋፍ የሚውል ሶስት ሚሊየን ብር በጀት በማጽደቅ ወደ ተግባር መገባቱ ተጠቅሷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.