Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛ ፖሊስ ሳይንስ ስልጠና ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 100 ፖሊሶችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛ ፖሊስ ሳይንስ ስልጠና ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 100 ፖሊሶችን አስመርቋል፡፡

ፖሊሶቹ ለአምስት ወራት በአካል ብቃት፣ በቴኳንዶ፣ በአድማ ብተና እንዲሁም በወታደራዊ ሰልፍና በወንጀል ምርመራ የሰለጠኑ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 617ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

መደበኛ ፖሊሶቹ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሲሆን፣ ሃገርን በጀግንነት ለመጠበቅና በሰብአዊነት ለማገልገልም ህገ መንግስታዊ ትምህርት የተሰጣቸውና ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሚናቸው የጎላ ይሆናልም ነው የተባለው።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውም ለተመራቂ ፖሊሶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.