Fana: At a Speed of Life!

በኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል  የተመራ ልዑክ ለስራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ገባ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ልዑካናቸው ለስራ ጉብኝት  ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል ።

የልዑካን ቡድኑ ጁባ የገባው በደቡብ ሱዳኑ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ሃላፊ ጄኔራል ማጃክ አከክ ግብዣ መሆኑ ተመላክቷል።

ሁለት የፖሊስ አዛዦች በሁለቱ አገራት ትብብር ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል ፡፡

በዚህም በድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ፣ በሁለቱም አገራት የፖሊስ መኮንኖች የመረጃ ልውውጥ እና ስልጠና መስኮች እንደሚወያዩ ከደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.