Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የፓርኩ የህብረተሰብና ቱሪዝም ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው አንደገለጹት በፓርኩ ትላንት ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል ።
ቃጠሎው በፓርኩ ከቧሂት ጀርባ አማረ ሸማ በተባለ ስፍራ መከሰቱን ተናግረው ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከትናንት ጀምሮ የደባርቅና የጃናሞራ ወረዳ ህዝብና አመራሮች እንዲሁም የፓርኩ የእሳት አደጋ ተከላካይ ብርጌድና ስካውቶችን በማሳተፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል ።
ቃጠሎው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመትም በተደረገ ጥረት በከፊል መቆጣጠር እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡
ቃጠሎው በጓሳ ሳርና በቁጥቋጦ ዛፎች ላይ እንደተከሰተ የጠቆሙት ሃላፊው የእሳት አደጋው መንስኤ እስካሁን በውል እንዳልታወቀ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.