Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ብሔራዊ ቡድኑን ለማጠናከር ሁለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ጠሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር አቻው ጋር የፊታችን ረቡዕ ጨዋታውን ደርጋል፡፡
ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድኑን ለማጠናከር ሁለት ተጨማሪ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን አካተዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ቡናው ወንድሜነህ ደረጀ እና የሰበታ ከተማው መሳይ ጳውሎስ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.