Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር አንደኛ ዙር የመኪና ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር አንደኛ ዙር የመኪና ውድድር በአዲስ አበባ አካሄደ፡፡

ውድድሩ በአራት ምድብ ተከፍሎ በ1000 ሲሲ 12 ተወዳደሪዎች፣ በ1300 ሲሲ ስድስት ተወዳዳሪዎች እንዲሁም በ1600 እና በ2000 ሲሲ 10 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚህ መሰረት በ1000 ሲሲ ሉካ ሚባሊደስ የዋንጫ እና የ5 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ሲሆን 2ኛ ደረጃ  ለወጣው  እስጢፋኖስ ቫሊሪ  የ3 ሺህ ብርና የዋንጫ  እንዲሁም 3ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቀው  ሄኖክ እቁባይ የ2  ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በ1300 ሲሲ 1ኛ ለወጣው አንተነህ በላቸው የ5 ሺህ ብርና ዋንጫ፣ 2ኛ ለወጣው ጎይቶም አለማየሁ የ3 ሺህ ብርና ዋንጫ፣ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቀው አባይ ብዙነህ የ2 ሺህ ብር እና ዋንጫ ተሰጥቷል፡፡

በ1600 ሲሲ ኢሚሊዬ ግራፊ 1ኛ በመውጣት የ5 ሺህ ብር እና ዋንጫ፣ በተመሳሳይ 2ኛ ለወጣው ለወጣው ሮቤል ጌታቸው የ3 ሺህ እና 3ኛ ለወጣው ብሩክ አማረ ፣ የ2 ሺህ ብር እና የዋንጫ  ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በ2000 ሲሲ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡት ዳዊት ተሾመ፣ አበበ ጌታቸው፣ ቢኒያም ዘሪሁን  ለእያንዳንዳቸው የ5 ሺህ፣ የ3 ሺህ እና የ2 ሺህ ብር እና ዋንጫ እንደተበረከተላቸው ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.