Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የፓርኩ የኅብረተሰብ እና ቱሪዝም ኃላፊ ታደሰ ይግዛው ከትናንት በስተያ የተነሳው እሳት በኅብረተሰቡ እና በፓርኩ ሠራተኞች ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ያስታወቁት፡፡

በፓርኩ ገደላማ አካባቢዎች የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡

የእሳት ቃጠሎ በሳሩ ላይ እና በአንዳንድ ዛፎች ላይ የተወሰነ ጉዳት ከማድረሱ በስተቀር በዱር እንሰሳት ጉዳት ያለመድረሱን ጠቅሰዋል፡፡

በፓርኩ መሰል ችግሮች ሲከሰቱ ፈጥኖ ደርሶ ችግሮችን ሊቆጣጠር የሚችል የእሳት ቃጠሎ ብርጌድ ከዚህ በፊት መቋቋሙን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ቃጠሎውን በቀላሉ መቆጣጠር በመቻሉ ብርጌዱ ወደ ሥራ አልገባም ነው ያሉት ኃላፊው፡፡

የእሳት ቃጠሎው መነሻ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም ብለዋል፡፡

መሰል ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው ቢከሠት መቆጣጠር እንዲቻል የአካባቢውን ማኅበረሰብ እንደተደራጀ አብመድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.