Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ በመዲናዋ ብሄርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሊፈፀም ነው የሚል ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ የትስስር ገፆች ብሄርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሊፈፀም ነው የሚል ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን አስጠነቀቀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ በአንዳንድ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የህብረተሰቡን በጋራ አብሮ የመኖር እሴቶችን የሚያናጉ ሀሠተኛ መረጃዎች እየተሠራጨ ነው ብሏል።

በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ ነገር ግን የፖሊስ መታወቂያ የሌላቸው ጸጉረ ልውጥ ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ ብሔር እና ሃይማኖት በመመዝገብ ላይ ናቸው ብሏል ፖሊስ።

እነዚህ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጸጉረ ልውጦች የተወሰኑ ብሔሮችን እና ሃይማኖቶችን ለይተው ለማጥቃት እየተንቃሰቀሱ ነው የሚሉ እና በነዋሪው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሃሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን ኮሚሽኑ እንደደረሰበት ገልጿል።

ፖሊስ በፀረ ሠላም ሀይሎች እየተሠራጨ ያለው ሀሠተኛ መረጃ ህብረተሰቡን ለማደናገጥ እና ለማሸበር እንዲሁም ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እንዲሁም በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ስጋት ለመፍጠር ሆን ተብሎ ታቅዶና ታስቦ እየተሰራጨ ያለ ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲል ገልጾታል፡፡

በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ በስፋት የተሰራጨ በመሆኑ በሰዎች የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ የስነ ልቦና ጫና እያሳደረ ነው፡፡

በመሆኑም ከተገቢው አካል መረጃ ሳይጠይቁና ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጩ እንዲሁም መረጃን ተቀብለው የሚያናፍሱ አካላት ከህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ከተማዋ ላይ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግና በማጣራት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት መደበኛ ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ እንደሚገኙ እና ነዋሪውም የእለት ተእለት ተግባሩን እያከናወነ መሆኑን ነው ኮሚሽኑ የገለፀው ፡፡

ህብረተሰቡ በፀረ- ሰላም ኃይሎች የሚናፈሱ መረጃዎች ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን በመረዳት ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የከተማዋን ፀጥታ አስመልክቶ የሚተላለፉ መረጃዎችን በተመለከተ ከተገቢው አካል የሚለቀቁ መረጃዎች ሊከታተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ለጸጥታ ስራ እያበረከተ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን በማቅረብም የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲገጥመው ጥቆማ ለመስጠት ነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11መጠቀም እንደሚቻልም መልዕክት አስተላልፏል ።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.