Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት 200 የአካቶ ትምህርት መስጫ ማዕከላት መቋቋማቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በዚህ ዓመት 200 የአካቶ ትምህርት መስጫ ማዕከላት መቋቋማቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በልዩ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት ዙሪያ ለርዕሰ መምህራንና ተዘዋዋሪ መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ አዳዲስ ማዕከላት መቋቋማቸውንም አመላክቷል።

እያንዳንዱ ማዕከላት እስከ 35 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ናቸው ተብሏል።

ስልጠናው የተሰጠው ርዕሳነ መምህራንና ተዘዋዋሪ መምህራንን ማዕከላቱን በአግባቡ በማደራጀት በተገቢው መንገድ መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑንም በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክተር አቶ ተኽላይ ገብረሚካኤል ተናግረዋል፡፡

ይህም በሃገሪቱ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ህጻናት የመማር መብታችው እንዲረጋገጥ የተያዘው ጥረት አካል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.