Fana: At a Speed of Life!

ዓለም እየተጋፈጠች ለምትገኘው ችግር ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች አስፈላጊዎች ናቸው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓለም እየተጋፈጠች ለምትኝ ችግር ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች አስፈላጊዎች መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የገንዘብ፣ እቅድ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች 53ኛ ጉባዔ ላይ በተሳተፉበት ወቅት ነው፡፡

በመክፈቻ ንግግራቸው ዓለማችን እየተጋፈጠች ከምትገኘው ተፈጥሯዊ እና ሰብዓዊ ነውጦች ጋር ተያይዞ፣ ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች አስፈላጊ መሆናቸው የአጀንዳውን ወቅታዊነት እንደሚያሳይም ገልጸዋል፡፡

አፍሪካ የኮቪድ19ኝን ቀውስ በመጋፈጥ ሂደት ውስጥ የመቋቋም ችሎታዋን ከማሳየት ባለፈ መፍትሄዎችን ለመቅረፅ እና ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየችውን አቅም እና ዝግጁነትም አድንቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ አቅጣጫዎች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተኮር ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ማዕቀፎችን ለትግበራ በሚያመች መንገድ ማብቃት ላይ ማተኮራቸው እጅግ  አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.