Fana: At a Speed of Life!

የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርጫፍ  አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርጫፍ  በአዲስ  መልክ በማደራጀት  አገልግሎት መስጠት መጀመሩን  አስታውቋል።

ቅርጫፉ ቀደም ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር ጉርድ ሾላ ቅርጫፍ በሚል ስያሜ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን÷ በአሁን ወቅት የለሚ ኮራ ቅርጫፍ በሚል ተቀይሮ ነው አገልግሎት መሥጠት የጀመረው።

የቅርጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አስፋው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገተጹት÷ ቅርንጫፉ በሰው ሀይል 90 በመቶ በማደራጀት ስራ መጀመራቸውን ነው የገለጹት ።

በዚህም ቅርንጫፉ የውሀ ስርጭት ዝርጋታ ፣ ውዝፍ  ክፍያ፣ቆጣሪ ንባብና ሌሎችንም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ነው ያሉት

ቀደም ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር የነበሩ ወረዳ 8 ፣9 ፣10  ፣ 11 እና 15  በዚሁ ቅርጫፍ ስር መካተታቸውን አመላክተዋል።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.